Mihret Kebede
#evolutionarypoems78
ሸዋ በጎጠኛ ……. እንዲህ ሳይንጋደድ
ያንዱ ድል ለሌላው ሳይሆን የጠብ መንገድ
የሰው ሃሳብ ልኩ….ጠቦ መንደር ሳይወርድ
ላ'ገር ሞተው ነበር …… እነ ሸዋ ረገድ፤
ሸዋ ረገድ ገድሌ
የነጻነት ሎሌ
ወዲህ ዝለቂና ……ላውጋሽ ያገር ምስጢር
ወደፊት እያለ …….ኋላ ቀርቷል እግር
ያኔ ላገር ሲ’ሞት….እንዴት እንዴት ነበር ???
ባ'ድዋ ማግስት ቆሜ ….ድልሽ ይሸተኛል
ደግሞ እዚያው ላይ ሆኜ ጠብ ጠብ ያገሳኛል
ወልጣቀኙ ሀገሬ …… ሳይበስል አሮብኛል
አንድ ሀገር ላይ ሆኜ….አንድነት ጠፍቶኛል፤
ውዴ ሸዋ ረገድ …..
ምንድነው አድዋ ……ምንድነው ሶሎዳ
ሰው ሰውን ሊያከብር …ሰው ታምር ባይሰራ
ማን ያወጣለታል …….ስሙን ለተራራ ???
በይና በያቸው …..
መኖር ማ’ኖር እንደሁ…..ቢገለጥላቸው ፤
ጣይቱ ለምዬ …..ጥበብ ባትገብር
ለጃገማ ኬሎ…..ሸዋረገድ ባትኖር
ድልን ማን አንዳሻው…. ይፎክራት ነበር ???
ውዴ ሸዋ ረገድ …..
የተጠማጠምሺው …ገድልን እንደ ገመድ
አለም ገና ሆነሽ ….እኔ አለም ጥግ ሆኜ
ሰው መሆን ቻልኩብሽ ሰው ሀገር ላይ ሆኜ
ውዴ ሸዋ ረገድ
ይሄውልሽ መውረድ….
አለም ገና ገና …… ሀገር ገና ገና
አለም ገና ገና …… ገድል ገና ገና
በወንድ የተሰራው …ጉልበቱም አልጠና
ያንቺን አይነት ገድል ….. አይከትብምና
ያንቺን ዓይነት መሆን ….አልታደለምና ::