Mihret Kebede
አቃጅ
语言: 阿姆哈拉文
翻译:
英文 (The Planner)
አቃጅ
ቢሆን ባይሆን ብሎ …..ማቀድ ለምንድነው?
ሰው መሆን በራሱ …..ያቃጁ እቅድ ነው
አቀጁ ካለበት…. እቅዱን እስኪያጸድቅ
አልያም ተጸጽቶ ….. ዶሴውን እስኪቀድ
እንደ ጅረት ውሀ ዝ….ም ብሎ መፍሰስ ነው
አፈሳሰስ ደግሞ….. ፍቺው ለየቅል ነው
አንድም ቋጥኝ መዝለል….. መ ፈ ነ ጣ ጠ ር ነው
አልያም ጎዳና ላይ ….. ድንጋይ ስር መቅረት ነው ::