Mihret Kebede
#evolutionarypoems132
የለሽም እንዳልል ..... ሰንደቅሽን ሰቅለሻል
አለሽም እንዳልል ..... መኖር ሞቶብሻል
እንዳገር እንዳገር.... ደርሶ ይሰራራሻል
እንደ ህዝብ እንደ ህዝብ..ተንጠሽ አልቀሻል
በየቀኑ እየዳህሽ ..... ተስፋዬን ገለሻል ፤
ተደበቂ ሀገሬ ....እርም የለም ዳስ ጥሎ
ሟች ገዳዩን ሳያውቅ....ከውድማ ተጥሎ
ካውሬ እየተጠጋ....ከሰው ግፍ ኮብልሎ
እንዴት ነው 'ሚለቀስ...ፍራሽ አደላድሎ?
በሚፎክር ዘመን... ድሀን ዳግም ገሎ ።