Mihret Kebede
#evolutionarypoems149
Язык: амхарский
Переводы:
немецкий (#evolutionsgedichte149)
#evolutionarypoems149
ሀብታም ገንዘብ አለው...ሹም ይገዛበታል
ሹምም ስልጣን አለው...ሀብታም ያዝበታል
በሞቴ በሞቴ እየተባባሉ
የምስኪን ደጅ ላይ... እጅ ይታጠባሉ
ከመንደርህ ዘልቀው... መሬት ይለካሉ
በዛፍ በቅጠሉ....ሀብት ይማልላሉ
አንተ 'ማትበላበት...ሆቴል ይከፍታሉ
ጥምህን የማይቆርጥ...ካፌ ያስመርቃሉ
ከስር ያውሉሀል ... ስራ እድል እያሉ
ገዢና ተገዢን.... በቀን ያመርታሉ
ምን ይገዳቸዋል.... ኢንቨስተር አይደሉ ¡¡