Mihret Kebede
#evolutionarypoems140
Язык: амхарский
Переводы:
немецкий (#evolutionsgedichte140)
#evolutionarypoems140
ወታ'ደር ነኝ እኔ... ሟች ላሳዳሪዬ
አንተ ቤት እንድታድር....እኔ ከዱር ውዬ
የምንወራረድ ....ባ'ገር ፊት በዶሴ
አንተ በሺህ ምላስ.... እኔ ባንድ ነፍሴ ፤
ያገር ልጅ ነህ አንተ.... ቃልህን የምትሰጥ
አንዱ ቃል ሲከዳህ ...ባንዱ የምታመልጥ
ያገር ልጅ ነኝ እኔ .... ተጓዥ በ'ሳት ረመጥ
አንድ "ሩሄን" ይዤ .... እሷኑ የምሰጥ
ወቶ-አደር ነኝ ላንተ... "ልጅ" ለወላጆቼ
ድልን የማላያት..."ድል" አድርጌ ሞቼ ።