Mihret Kebede
#evolutionarypoems127
ዲ'ሳባ ነገረ ....እንደ ህልም እንደህልም
እሳት መሀል ሆኖ.... እንደሚስለመለም
እንቅልፍ መሀል ሆኖ ....ንቃት እንደማለም፤
አውቆ እንዳላወቀ....አይቶ ማንቀላፋት
ጧ'ቱን ዱካክ ደፍቶት...ቀትር ላይ መባተት
ይሁን እስኪ ብሎ..... 'ሚሆኑትን ማየት፤
ያዲሳባ ነገር...እንደ ህልም እንደህልም
ልክ እንደ ሰመመን...ነቅቶም እንደሚያልም
የነጋ በሚመስል...በማይነጋ ንጋት
ሸር ተ ተ ት እያሉ....ቀስ እያሉ መንቃት
አልጋ ላይ ነኝ ብሎ...መሬት ላይ መገኘት
ይመስላል እንደ ወንዝ መፍሰስም እንደቃል
ታግሶ ታግሶ.... ደራሹን ማን ያውቃል?