Mihret Kebede
#evolutionarypoems115
Язык: амхарский
Переводы:
немецкий (#evolutionsgedichte115)
#evolutionarypoems115
ሰው ከሌለ ለወንዝ …..ማን ይዘፍንለታል
ስሙንስ ለውሃ…….. ማን ያወጣለታል?
አባይ እንኳ ራሱ ……የድሮው አይደለም
አሁን የወረደው……. "ዞር" ስትል የለም
ያ...ኔ የዘፈኑለት …..ለዚህ ውሃ አይደለም
ይነጉዳል ወደፊት ….ጅረት እየተካ
አንተ እና እኔ ቆመን….. ጉልበት ስንላካ
ከፍ ያለ የመሰለው ….ምስኪኑን ሲከካ።