Mihret Kebede
የሀገሬ ባሎች
Язык: амхарский
Переводы:
английский (Husbands of My Dear Country)
የሀገሬ ባሎች
እስኪ ሀገሬ …..ልግጠምልሽ
የኔ መግጠም….. ከጠቀመሽ፤
እንደ ባለቅኔ …. ባልገጥምልሽ እንኳን
እንደ’ክት ባሎችሽ …. ባልሆንልሽ እንኳን
ያልራሰውን መሬት…… በላቤ እንዳለማ
ባ’ጥር እየሾለኩ….. ልሁንሽ ውሽማ፤
እንጂ በርሽማ
የላይ የላዩማ
ላይገጥምሽ ተዘግቶ
ላይሆንሽ ተጣብቶ
ማንን አስገብቶ?
ቢሆንም ቢሆንም ….. ላግባሽ ባልልሽም
እስኪ ሀገሬ ልግጠምልሽ
የኔ መግጠም ከጠቀመሽ ፤
መች ይቀራል…. መግጠሜማ
ሰባስቤ ….የቃል ማማ
የህዝብ ግጥም…. የህዝብ ዜማ፤
ግና እኔ ደርሼ …..ቶሎ እስክገጥምልሽ
ሀረግ ጠማጥሜ ….ቤት እስክመታልሽ
ቀለበት አጥልቄ …. የሁሉ እስካደርግሽ
ሰምሽ እዜህ ማዶ….ወርቅሽ እዚህያ ማዶ
ህብረ-ቃልሽ ሁሉ…. ከባእድ ተሰዶ
የድስትሽ ክዳኑ…. ሳይገጥም ተንከርፍፎ
በኔ እገጥም ……በኔ እገጥም…. ገላሽ ብርድ አትርፎ
ወጥሽ እኮ አለቀ ….. ተጨልፎ ተጨልፎ ::